Friday, 27 September 2024

ስልጣንና ተግባራት

የኮሚሽኑ ስልጣንና ተግባራት

  • በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉት የአካባቢ ደህንነት ዓላማዎችና በአገሪቱ የአካባቢ ፖሊሲ የተመለከቱት መሠረታዊ መርሆዎች ከግብ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን ያስተባብራል፣
  • በመንግሥትም ሆነ በግል የሚወጠኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ፖሊሲዎች፣ሥልቶች፣ሕጎች፣መርሀ ግብሮች እና ፕሮጀክቶች ላይ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ወይም ስልታዊ የአካባቢ ግምገማ ለማካሄድ የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፤ሥርዓቱ በተግባር ላይ መዋሉንም ይከታተላል፣
  • ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ፍትህን በሚያራምድ እና ከሚገኘው ጥቅም ትልቁን ድርሻ በእርምጃው ለሚነኩ ማህበረሰቦች በሚያስገኝ የስርየት እርምጃ ከደን ምንጣሮና ጉስቁልና ሊከተል ይችል የነበረውን ሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት የመቀነሻ ስርዓት ያዘጋጃል፡፡
  • ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን በየዘርፉና በየክልሉ ለመገንቢያ የሚውል ሃብት የሚያስገኙ ተግባራት ዝግጅትን ያስተባብራል፣ የአቅም ግንባታና ድጋፍና የምክር አገልግሎትን ይሰጣል፡፡
  • በአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ መሠረት ለልማት ፕሮጀክት እና ፕሮግራም የይሁንታ ፈቃድ ከመሰጠቱ በፊት የፕሮጀክቱ እና የፕሮግራሙ ትግበራ በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተፅዕኖ በሚመለከተው የዘርፍ የፈቃድ ሰጪ አካል ወይም በሚመለከተው የክልል አካል ተገምግሞ ውሳኔ የሚሰጥበትን ሥርዓት ይዘረጋል፣ትግበራውንም ያረጋግጣል፣
  • ኢትዮጵያ ከተፈጥሮ ሃብቶች መሠረት፣ከበረሃማነት፣ከደን፣ከአደገኛ ኬሚካሎች፣ከኢንዱስትሪ ቆሻሻዎች እና ከሰው ሰራሽ የአካባቢ አደገኛ ንጥረ ነገሮች ጋር በተያያዘ የፀደቀቻቸው አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የአካባቢ ስምምነቶችን በየዘርፉና በየአስተዳደር እርከኑ በመተግበር ወቅት የድግግሞሽ፣ የሃብትብክነትንና ክፍተትን ለማስቀረት የሚያስችሉ መርሀ-ግብሮችን እና መመሪያዎችን ያዘጋጀል፣መተግበራቸውንም ይከታተላል፣
  • በዓለም አቀፍ የአከባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነቶች ድርድር ላይ ይሳተፋል፣ በዘርፉ አገራዊ ምላሽን በማስተባበሩ በኩል ቁልፍ ሚና ይጫወታል፣እንደ አግባቡ ስምምነቶቹ እንዲፀድቁ ሃሳብ ያቀርባል፣
  • ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸውን ዓለም አቀፍ የአካባቢ ውሎች ለመተግበር ተፈላጊ የሆኑ ፖሊሲዎችን፣ ስልቶችን፣ ሕጎችንና መርሀ-ግብሮችን እንደሁኔታው ያዘጋጃል፤እንዲዘጋጁ ሃሳብ ያመነጫል ፣አዘገጃጀታቸውን ያስተባብራል፣ ሲፈቀዱም በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፣
  • አደገኛ ንጥረ ነገሮችን ወይም ዝቃጮችን ማምረትን፣ወደሀገር ውስጥ ማስገባትን፣አያያዝን እና አጠቃቀምን እንዲሁም ሕያዋንን በዘረመል ምህንድስና መለወጥን ፣ልውጥ ወይም ባዕድ ሕያዋንን ወደ አገር ማስገባትን ፣አያያዝና አጠቃቀምን የሚመለከቱ የአካባቢ ደህንነት ፖሊሲዎችን እና ሕጎችን ያዘጋጀል፤በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፣
  • በልማት ዕቅዶችና በኢንቨስትመንት መርሀ-ግብሮች ውስጥ የሚካተቱ የአካባቢ አዋጪነት ማስሊያ ቀመሮችንና የስሌት ሥርዓቶችን ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤እንደሁኔታውም በጥቅም ላይ የመዋላቸውን ሂደት ይከታተላል፣ዘላቂነት የጎደለው የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀም ልምድን፣ የአካባቢ ጉስቁልናን ወይም ብክለትን ለመከላከል በሚያስችሉ የመግቻ እርምጃዎች ወይም የማበረታቻ ዘዴዎች መጠቀምን በተመለከተ ሃሳብ ያቀርባል፣
  • የአካባቢ መረጃ አሰባሰብን፣አደረጃጀትን እና አጠቃቀምን የሚያቀላጥፍ የአካባቢ መረጃ ሥርዓትን ይዘረጋል፣
  • የአካባቢና የደን አያያዝን፣በጥቅም ማዋልንና ፍትሃዊ የጥቅም ተጋሪነትን የሚያራምድ እንዲሁም አረንጓዴ የስራ ዕድልን የሚፈጥር ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ያስተባብራል፣እንደ አስፈላጊነቱ ራሱ ያካሂዳል፣
  • አግባብነት ባላቸው የሕግ ድንጋጌዎች መሠረት የአካባቢና የደን ጥበቃ ግዴታዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ በፌዴራሉ ሥልጣን ሥር ወደሚገኝ ማንኛውም መሬት፣ቅጥር ግቢ ወይም ሌላ ቦታይገባል፣ኃለፊነቱን ለመወጣት ተገቢ ሆኖ ያገኘውን ማንኛውም ነገር ይፈትሻል፣ናሙናዎችን ይወስዳል፣
  • የሀገሪቱን የአካባቢና የደን እንዲሁም ለአየር ንብረት ለዉጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን በሚመለከት ዘገባን በየወቅቱ እያዘጋጀ ያሰራጫል፣
  • መደበኛ ያልሆኑ የአካባቢ ትምህርት መርሃ- ግብሮችን ያስፋፋል፣ትምህርቱን ይሰጣል፣የአካባቢ ጉዳዮችን በመደበኛ ትምህርት ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ ለማካተት አግባብ ካላቸው መስሪያ ቤቶች ጋር ትብብር ያደርጋል፣
  • አነስተኛና ሰፋፊ የደን ልማት፣ቀርከሀን ጨምሮ በግል፣በወል ይዞታ እና በተፋሰስ ውስጥ እንዲለማና ጥቅም ላይ እንዲውል ሥርዓት ይዘረጋል፣ትግበራውንም ያረጋግጣል፣
  • የሀገሪቱ የተፈጥሮ ደን እንዲጠበቅና እንደአስፈላጊነቱ ዘላቂ ጥቅም ላይ እንዲውል ሥርዓት ይዘረጋል፣ትግበራውንም ያረጋግጣል፣
  • የተጎዱና የተራቆቱ የደን መሬቶች እንዲያገግሙና የአካባቢያዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው እንዲሻሻል ሥርዓት ይዘረጋል፣ትግበራውንም ያረጋግጣል፡፡
  • ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር ተያያዙ ሥራዎች ይካተታሉ…

 

 

 

የባለስልጣንኑ አድራሻ

አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከአብርሆት ቤተመጻሕፍት በስተጀራባ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አጠገብ፣ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9

ስልክ፡ +251 (0)11-170-4038/4150

ፋክስ፡ +251 (0)11-170-4158/ 45

ኢመይል   Info@epa.gov.et

ቲውተር  https://twitter.com/epaethiopia

ፌስቡክ   https://www.facebook.com/MefEth/

ቴሌግራም   https://t.me/efcccethiopia

..      12760

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ