የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ‘’ወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲቲዩት’’ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር የስርዐተ-ምዳር ግልጋሎት
* ምንነት?
* ዓይነት?
* እንዴት የስርዐተ-ምዳር ግልጋሎት ክፍያ እንዴት መተመን እንደሚቻል እና ሌሎች ተጓዳኝ ርዕሶችን በማንሳት ከክልሎች እና ከፌዴራል ተቋማት ለተወጣጡ ሙያተኞች ለአራት ቀን የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ ፡፡
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የአካባቢ የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ባለሙያ አቶ ጥላዬ ንጉሴ የስ-ነምህዳር ግልጋሎት ክፍያን ስናስብ በዋናነት አተኩረን መስራት ያለብን ሁሉን አቀፍ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ እና አጠቃቀም ላይ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በእለቱ ስልጠና የስ-ነምህዳር ግልጋሎት ክፍያ እና ትመናን አስመልክቶ ታሪኩ ምን እንደሚመስል ? ከኢኮኖሚ ጋር ምን እንደሚያገናኘው ? የስ-ነምህዳር ግልጋሎት ክፍያ አተማመንን ? እንዲሁም ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ ህጋዊ እና ተቋማዊ አደረጃጀቶችን አስመልክቶ ከሀገር ውስጥ እና ከአለማቀፍ ተቋማት በተጋበዙ አሰልጣኞች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የእለቱ መድረክ ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ተጠናቋል ፡፡
መድረኩ በቀጣይ የተለያዩ ርዕሶችን በማንሳት ለተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡