በኢትዮጰያ አካባቢ ጥበቃ ባስልጣን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ።
መጋቢት 2016ዓ.ም,ቢሾፍቱ
በበዓሉ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮች እንዲሁም ሴት ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው እንደገለጹት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአለም ለ113 ጊዜ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለ48ኛ ጊዜ ''ሴቶችን እናብቃ;ልማትና ሠላምን እናረጋግጥ" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ እንደሚገኝ ጠቁመው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ አለምአቀፍ ጉዳይ በመሆኑ የቁጥጥር ስራዎች በየደረጃው እየተተገበሩ እንደሚገኙ ገልፀው በዚህም በዓለምአቀፍ ብሎም በሀገራችን ያሉ ፓሊሲና ህጎች ሴቶችን አሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርጉ በመሆናቸው ሴቶች ተሳትፏቸውን በማሳደግ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሴቶችና ማህበራዊ አካትቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ መጫ በበኩላቸው በዓሉን ስናከብር የመስሪያ ቤቱን የሴቶች ፎረም መልሶ በማደራጀት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅ ገልፀው ሴቶች ወጣቶችንና አካልጉዳተኞችን አካታች በሆነ መንገድ ለችግሮች መፍትሄ በመሻት ጠቃሚ ውሳኔዎችን ለመወሰን በቅንጅትና መናበብ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የብዙኀንን ሴቶች ህይወት እየቀጠፈ ያለው የጡት ካንሰር ላይ ከጤና ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች ግንዛቤ በመፍጠር የበጎ ፍቃድ የጡት ካንሰር ምርመራ ተከናውኗል።