በኢትዮጵያ የደን ዘርፍን መዋቅራዊና የስርዐት ለውጥ ዘላቂነት ወዳለው ደረጃ ለማሸጋገር ባለመው የቀጣይ የአስር አመታት መሪ እቅድ ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በሀገራችን የደኑን ዘርፍ ዘላቂነት ባለው መልኩ ለማልማት፣ ለመጠበቅና ለኢኮኖሚ ፋይዳ ለማዋል ያለመ የአስር አመት እቅድ ተዘጋጅቶ ባለፈው ዓመት ስራ ጀምሯል፡፡ ይህንኑ የልማት ስልት መዘርጋት ተከትሎ የደን ዘርፍ ልማት ትራንስፎርሜሽን ዩኒት በኮሚሽኑ የደን ዘርፍ ስር ተደራጅቷል፡፡
የደኑ ዘርፍ ባለፉት በርካታ ዘመናት ለሀገራችን ኢኮኖሚና ለህዝቡ የማይተካ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያበረከተና በማበርከት ላይ ያለ ቢሆንም ሀገራችን በዘርፉ ካላት እምቅ አኳያ ሲለካ ግን አጥጋቢ ካለመሆኑም አልፎ ዘርፉን እየተፈታተኑ ከመጡ ተግዳሮቶች አዳዲስና ሳይንሳዊ የሆኑ አማራጮችን መተግበር መተኪያ የሌለው ጉዳይ መሆኑ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡
በ1999 ዓ.ም ወጥቶ በትግበራ ላይ በቆየው የኢትዮጵያ የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ፖሊሲ ላይ ከተለዩትና እስካሁንም ከዘለቁ ተግዳሮቶች መካከል፡-
* ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የህዝብ ቁጥር መጨመር(የመስፈሪያ ስፍራ ወደ ደን ክልል
መግባት)፤
* ለአዝእርት እርሻ ሲባል የደን መመንጠር፤
* የማገዶና የኮንስትራክሽን ፍጆታ መጨመር፤
* ህገ ወጥ የደን ቆረጣና የህገ ወጥ ንግድ መስፋፋት
በግንባር ቀደምነት የተለዩ ሆነዋል፡፡
ይህንን የፖሊሲ ማዕቀፍ ታሳቢ በማድረግ የደኑን ዘርፍ ልማት ለማስፋፋት፣ ለመጠበቅና ጠቀሜታውን ለማሳደግ የተለያዩ ስትራተጂዎችና ፕሮግራሞች ተቀርፀው ሲተገበሩ መቆየታቸውና እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡
1ኛ. የደን ዘርፍ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት፡-
ይህ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የዘርፉን አቅም በማጎልበት ሲሰራ የቆየ ሲሆን በዋናነትም፡-
* በተመረጡ 54 ወረዳዎች ላይ 75,000 ሄክታር የተራቆተ
መሬትን በማህበረሰብ ተሳትፎ አልምቷል
* አሁንም በሂደት ላይ አለ፣
2ኛ. ሬድ ፕላስ ሲክሬተርያት(REDD+ Secreteriat):-
ይህ ስትራተጂካዊ እርምጃ ኢትዮጵያ በ2011 አውጥታ ለአለም ማህበረሰብ ያስተዋወቀችውና "የአረንጓዴ ልማት ስልት-CRGE" ተብሎ የሚታወቀውና በአራት መሰረታዊ ዘርፎች (ግብርና፣ የሀይል ዘርፍ፣ የደን ዘርፍና የትራንስፖርት ዘርፍ) እና ሌሎች ከሚባሉ ዘርፎች እስከ 2025 የአንድ መቶ አርባ ሰባት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ኢኩቫለንት የሙቀት አማቂ ጋሶች ልቀትን ለመቀነስ ቃል ተገብቷል፡፡
በዚሁ መሠረት ከደን ዘርፍ ብቻ እ.አ.አ. እስከ 2030 ድረስ 130ሚሜ ቶን ጋስን ከደን ዘርፍ ብቻ ለመቀነስ ያለመው የሬድ ፕላስ ስትራተጂ በ3 ምዕራፎች (የዝግጅት፣ የትግበራና የሙቀት አማቂ ጋሶችን ቀንሶና አረጋግጦ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማዕቀፋዊ ስምምነት የማሳወቅ ሀላፊነት የተጣለበት ሲሆን ይህም የሚከናወነው የደን ጭፍጨፋን በመግታትና የተራቆቱ/የተመናመኑ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ በማድረግ ነው፡፡
3ኛ. የደን ልማት ትራንስፎርሜሽን ዩኒት፡-
ይህ ዩኒት በደን ዘርፍ እ.አ.አ. ከ2018 ጀምሮ ለቀጣይ አስር ዓመታት በ3 የተለያየ መዳረሻ ዒላማዎች(3 phased volumes)እንዲተገበር የተቀረፀ ሲሆን በዘርፉ ሊያስገኝ የለያቸው ውጤቶችም፡-
* በቀጣይ 10 አመታት የሚተገበርና ግልፅ መዳረሻ ግብ ያለው ተቋማዊ አቅምን በማጎልበት የደን ዘርፍን በዘላቂነት ማልማትና ማስተዳደር፣
* በተራቆቱ የመሬት አካላት የተሻለ የደን ሽፋን እንዲኖር ማስቻል፣
* የተሻሻለ የብዝሀ ህይወትና ስርዐተ ምህዳር እንዲፈጠር መስራት፣
* የተሻሻለ የአፈርና ውሀ ሀብት ጥበቃ፣
* በማህበረሰብ ደረጃ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ የድርቅ ተጋላጭነትን መቋቋም
የሚያስችል አቅም መፍጠር እና፣
* ለሴቶችና ወጣቶች በዘርፉ የስራ እድልን መፍጠር እንዲችል ሆኖ የተቀረፀ ነው፡፡