የካቲት 8 ቀን 2016 የተጀመረው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ስልጠና በዛሬው ዕለት ተቋማዊ የስራ ባህል፣ የለውጥ አመራር እና ውጤታማ የቡድን ስራ ማጉልበትን ትኩረት ባደረጉ ርዕሶች ዙሪያ ቀጥሎል፡፡
እየተካሄደ ባለው ስልጠና በስራ ቦታ አመራሩ ሞዴል በመሆን መላው ሰራተኛን በማስተባበር መንግስትና ህዝብ ከተቋሙ የሚጠብቀውን ውጤት ለማምጣት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው እና መልካም የስራ ባህልን ተቋሙ ውስጥ በመገንባት በቀጣይ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተብራርቷል፡፡ በዚህም ዘላቂነት ያለው የአካባቢና ስርዓተ ምህዳር አጠቃቀም ስርዓትን በመገንባት ሀገራችን የሰነቀችው አፍሪካዊ የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ እውን ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ቁጥጥር ስራን ማጠናከር ተገቢ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በስልጠናው እየተሳተፉ ያሉ አመራሮችም በአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ የተነሱ አነቃቂ ጭብጦችን ወደ ተቋምና ግለሰባዊ ስብዕና ግንባታ በመውሰድ በቀጣይ በስራ ቦታ ላይ ለማዋል ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡