በአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን በተለያዩ የስራ ሀላፊነቶች ሲያገለግሉ የቆዩትና ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲከናወን የቆየውንና አመርቂ ውጤት የተመዘገበበትን "የአረንጓዴ አሻራ" ብሄራዊ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ሲመሩና ሲያስተባብሩ የቆዩት ዶ/ር ተፈራ መንግስቱ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው አልፏል።
ዶ/ር ተፈራ በስራቸው ታታሪና ለሌሎችም አርዐያ የሆኑ ባልደረባችን የነበሩ ሲሆን ባልታሰበ ወቅትና ሁኔታ ከመሀከላችን ስላጣናቸው ከፍተኛ ስብራትና መጉደል ተሰምቶናል።
የወንድማችንን ነብስ ፈጣሪ በአፀደ-ገነት እንዲያኖራትና ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንዲሰጣቸው ጥልቅ ሀዘናችንን በዘርፉ አመራሮችና ሰራተኞች ስም እንገልፃለን።
----------------------------®-----------------------------