የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በስራና በግል ህይወት የአስተሳሰብ ዘይቤ ማሳደጊያ የሚሆን የማነቃቂያ ስልጠና ለሰራተኞቹ ሰጠ፡፡ (የካቲት 14፣ 2016 ዓ.ም)
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ እንዳሉት እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎች የሰራተኞችን ተነሳሽነት ከማነሳሳት በላይ ጤናማ የሆነ የስራ ባህል እንደተቋም በመገንባት ላይ አዎታዊ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ክብርት ዋና ዳይሬክተሯም አያይዘው በማነቃቂያ ስልጠናው ላይ የተነሱ ጉዳዮችን በጥልቀት በመውሰድ በስራ ላይ እንዲሁም በግል ህይወታችን ውስጥ አመስጋኝነት፣ ቅናነት፣ ትህትና፣ አይበገሬነት እና መተማመን በመላበስ ለውጥን ለመተግበር ጥረት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዘበዋል፡፡
በመሆኑም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥራት ያለው አገልግሎት ለዜጎች መስጠት እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ተቋም ለማድረግ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ለዚህም ሁሉም አመራርና ሰራተኞች የበኩሉን እንዲያደርግ በማሳሰብ ስልጠናው በይፋ ዘግተዋል፡፡