የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የፕላስቲክ ቆሻሻ የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ።
ሚያዝያ 2016፣ አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የፕላስቲክ ቆሻሻ የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለስድስት ወራት በሚያካሄደው በፕላስቲክ:አየር:ውሀ:ድምፅ እና አፈር ብክለት ላይ የግንዛቤ መፍጠሪያ አድቮኬሲ አንዱ አካል በሆነው የፕላስቲክ ቆሻሻ ላይ የባለስልጣኑ ሰራተኞች በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የፕላስቲክ ቆሻሻ የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከሚያዝያ እስከ መጪው መስከረም 2016ዓ.ም የሚቆይ ሀገርአቀፍ የብክለት ቅነሳ ንቅናቄን ማስጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በያዝነው ሚያዝያ ወር የፕላስቲክ አጠቃቀም ዘይቤያችንን እናዘምን በሚል መሪ
ሀሳብ የተለያዩ የንቅናቄ ስልቶች በመጠቀም የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን የዛሬው የፅዳት ዘመቻም አንዱ ማሳያ ነው።
የወረዳ 9 ፅዳት አስተዳደር በወረዳ ደረጃ በየሳምንቱ የፅዳት ዘመቻ እንደሚካሄድ ገልፆ ይህንን አጠናክሮ ለመስራት እና ብክለትን ለመቀነስ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ላከናወነው ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ አቡኔ በበኩላቸው ፕላስቲክ በሰው በአካባቢ እና በእንስሳት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳለው በመግለፅ አጠቃቀምን በማዘመን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመስራት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ በመጠቆም ከንቅናቄው በኃላ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአካባቢ ጥበቃ ህግ ማስከበር ስራዎች እንደሚሰራ ገልፀዋል።
"ብክለት ይብቃ-ውበት ይንቃ"
የፕላስቲክ አጠቃቀም ዘይቤያችንን እናዘምን።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን