የዓለም የደን ቀን በዘንድሮ ዓመት በዓለማቀፍ ደረጃ ለ8ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ "FOREST and EDUCATION" በሚል መሪ ቃል በአምቦ ከተማ ተከበረ፡፡
በዐሉን በንግግር የከፈቱት የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ክቡር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ እንዳሉት የሀገራችን የደን ሀብት እንዲለማ፣ እንዲጠበቅና አስፈላጊውን ጠቀሜታ ለህዝባችን እንዲያበረክት መንግስት አስፈላጊ የሆኑ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ አክለውም እንደ ሀገር የደን ዘርፍ ለኢኮኖሚያችን የሚያበረክተውን ድርሻ ለማሳደግ በተለይም ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠርና ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
በበዐሉ ላይ ከተለያዪ ባለድርሻዎች የተሳተፉ ሲሆን በተለይም የዐመቱን መሪ ቃል "Forest and Education" የሚቸውን ዓላማ ከበዐሉ ጋር ለማስተሳሰር ሲባል በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በደንና ተያያዥ የትምህርት ዘርፎች ሚሰለጥኑ ተማሪዎች ጋር ተከብሯል፡፡
በተጨማሪም የክልሎች ተወካዮች፣ የልማት አጋሮች፣ ከዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ ምሁራን እና ሌሎች ባለድርሻዎችም ተሳትፈዋል
- በበዐሉ ላይ ሶስት ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን፡-የቀጣይ አስር ዓመታት የደን ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን መሪ ስትራተጂ፤
የደን ሀብትን የኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ እሴት ጨምሮ ለገበያ ማቅረብ ስለሚቻልበት ሁኔታ እና፣ - የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከደን ትምህርት አኳያ እያከናወነ ስለሚገኛቸው ተግባራት ዝርዝር ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም የበዐሉ ተሳታፊዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ ጥቅም የሚውሉ የደን ችግኞችን ስለሚያራባበትና የእውቀት ሽግግር ስለሚያከናውንበት ሁኔታ የመስክ ጉብኝት ተደርጓል፡፡