የጣሊያን መንግስት ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተመካከረ፡፡
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ-ጣሊያን መንግስታት የጋራ የልማት ትብብር ስራን ለማጠናከር የሚያስችል ጉብኝት በማድረግ ላይ ያለው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ሰራዎችን በሚያጠናክሩ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የረጅም ጊዜ የልማት ትብብር ስራን ሲሰሩ የቆዩ ሀገራት መሆናቸውን በመጥቀስ የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳዎች ዙሪያ ከጣልያን የአካባቢና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር ተጀምረው በኮቪድና በሌሎች ምክንያቶች ባለፉት ሶስት ዓመታ ተቋርጠው የነበሩ ፕሮጀክቶች በተለም አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚመለከቱ መሆናቸው ታሳቢ በማድረግ በድጋሚ እንዲቀጥሉ ስምምነት በተደረሰበት መሰረት በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገባ ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ስርዓተ-ምህዳር ተፈጥሮዊ ሂደት የመጠበቁ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ የስራ ዕድል ፈጠራን እንዲሆን ተጓዳኝ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች የሚያመጡ መሆኑን በመጥቀስ የጣልያን እና የሌሎች ሀገራትን አቅምና ልምድ ለመቅሰም ባለስልጣኑ ፍላጎት ያለው መሆኑን አንስተዋል፡፡