ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ የአየር ንብረት ተጋላጭነት ፎረም ላይ ንግግር አደረጉ፡፡ የፎረሙ ፕሬዝደንት በሆኑት የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚ/ር የተጠራዉ የመሪዎች ስብሰባ በተቀመጠዉ ቀነ ገደብ ዉስጥ መሪዎች የአየር ንብረት ለዉጥን ለመከላከልና ለዚህም ተገቢዉን እነቅስቃሴ ለማድረግ ያላቸዉን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡበት ነዉ፡፡
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ እንዳሉት “ ጊዜ የለንም፣ አገሮች ባላቸዉ አቅም ሁሉ እስከ ታህሳስ 2013 ዓ.ም. ድረስ የተቀመጠዉ ቀነ ገደብ ሳይደርስ ምላሽ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ቀነ ገደብ ዋነኛ የሆነዉን፣ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃዉን፣ እየባሰ የመጣዉን የአየር ንብረት ለዉጥን ለማስቆም የሚያስችል ነዉ፡፡ ከዚህም አልፎ በፓሪስ ስምምነት ላይ የሰፈረዉን የ1.5 ዲግሪ ሴልሲየስ ግብ ለማሳካት ይረዳናል፡፡”