ጉባዔው እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር ከአፕሪል1-4/2019 በአዲስአባባ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የጉባዔውን መከፈት በይፋ ያበሰሩት የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ 13ኛውን የማህበረሰብ አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ጉባዔን ለመታደም ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለመጡ አንግዶች በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ስም ወደ ሰው ዘር መገኛ ወደሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት ጉባዔው በኢትዮጵያ መካሄዱ በአየር ንብረት ማጣጣሚያ ስራዎች ላይ ከፍተኛ እውቀት ለማንሸራሸር የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ የአለማችን ከፍተኛ ስጋት መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸው በጉዳቱም ታዳጊ ሀገራት ከፍተኛ ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁመዋል ይህንን ስጋት ለመቋቋም ኢትዮጰያ ፈርቀዳጅ የሆኑ ተግባራትን በተለይም ለየአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን እ.ኤ.አ በ2011 (CRGE) እንዲሁም የአስራ አምስት አመታት ሀገር አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅድን እ.ኤ.አ በ2017 ይፋ በማድረግ በየደረጃው እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአለምአቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መድረኮችን በተለይም የዝቅተኛ በእድገት ደረጃ የሚገኙ ሀገራት (LDC) እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ሀገራት ፎረም (CVF) በሊቀመንበርነት ለሁለት አመታት መምራቷን እና አመርቂ ውጤት ማስመዝገቧን ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል፡፡
13ኛው የማህበረሰብ አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ጉባዔ በሶስት አጀንዳዎች ላይ ያተኩራል
የማህበረሰብ አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ የሚረዳ የሀብት ምንጭ ላይ ለማህብረሰብ አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን ማስረጽ ህግ አውጪ አካላትን ተሳታፊነት ማጠናከር ላይ ያተኩራል፡፡ በጉባዔው ላይ ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የመጡ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት፣ውሳኔ ሰጪ አካላት ፣ ህግ አውጪዎችና ባላድረሻ አካላት እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡
መጋቢት 2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ