ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በሀገራችን እያደገ ያለው የኢኮኖሚ እድገት እና የከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የቆሻሻ አይነትና መጠን እየጨመረ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ጋር በመተባበር የቆሻሻ አያያዝን ለማዘመን ሀገራዊ ሰርኩላር ኢኮኖሚ (ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ) ፎኖተ ካርታ ሰነድ የሚያዘጋጅ ፕሮጀክት የስራ ማስጀመሪያ አውደ ጥናት ተካሄደ ፡፡
አውደ ጥናቱን በንግግር ያስጀመሩት የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ለማ የተፈጥሮ ሀብትን በዘላቂነት ለመጠቀም ሰርኩላር ኢኮኖሚ (ቆሻሻን መልሰው መጠቀም) የኢኮኖሚ እድገት አቅጣጫን መከተል አመራጭ የሌላው መስመር መሆኑን በመግለጽ ሰርኩላር ኢኮኖሚ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሰራ አለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካለት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠይቀዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የፊንላንድ አምባሳደር ሚስ ሲኒካ አንቲላ ሰርኩላር ኢኮኖሚ አቅጣጫ መከተል ቆሻሻን በአግባቡ መያዝ ብቻ ሳይሆን ስራ እድል ለመፍጠር ፣ለኢኮኖሚን እድገት ፣ሙቀት አማቂ ጋዞችን ለመቀነስ እንደሚያስችል በመግለጽ ሀገራቸው በዘርፉ ያላትን ተሞክሮ ለማካፈል እና አቅም ለመገንባት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ ከጉዳዩ ጋር የሚገናኙ ጥናታዊ ጹሑፎች በባለሞያዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሄዷል ።
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
ድረገጽ https://epa.gov.et/
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/@epa-ethiopia258
ቴሌግራም https://t.me/efcccethiopia
ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/epaethiopia
ኢ-ሰርቪስ https://www.eservices.gov.et/provider/1065