ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ግንቦት 9/2016 ዓ.ም
አዲስ አባባ
ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማ የፌዴራልና የክልል ቢሮ ኃላፊዎች"፣የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣የፌዴራል ዘርፍ መስሪያ ቤት አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው ።
የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት ክቡር አቶ ስዩም መኮንን የፕላንና ልማት ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ አሁን ያለውን የአካባቢ ችግሮች ለመቀነስ መንግስት የአካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥን ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ዘርፉ በአዲስ መልክ መደራጀቱ፣ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አዳዲስ የአካባቢ ህጎችና ደንቦች እየወጡ መሆናቸውን አብራርቷል ።
አሁን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ እየተደረገ ያለው ሀገር አቀፍ የብክለት ቅነሳ ንቅናቄ፣ የአረንጓዴ አሻራ እና ጽዱ ኢትዮጵያ ዋና ዋና መሆናቸውን ገልጸዋል ።
የአካባቢ ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ብክለትን ለመቀነስ "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃል"በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳዳር ህብረተሰቡን ያሳተፈ እና በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል ። ንቅናቄውም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቴ ከሚመለከታው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ሲሆን ተጨባጭ ውጤቶችም እየተገኘ መሆኑን በመንሳት ሥራው እንዲሳካ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን በማመስገን በቀጣይም ጉድለቶችን በመቅረፍ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል ።
በመድረኩ ላይ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ የክልልና የከተማ መስተዳዳር የአካባቢ ጥበቃ የስራ ኃላፊዎች ተገኝቷል ።
👇ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
ድረገጽ https://epa.gov.et/
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/@epa-ethiopia258
ቴሌግራም https://t.me/efcccethiopia
ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/epaethiopia
ኢ-ሰርቪስ https://www.eservices.gov.et/provider/1065