ለፈቃድ እና የድጋፍ ደብዳቤ አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ
የኮሚሽን መ/ቤታችን የውጭ አግልግሎት ፈላጊ ደንበኞችን መመላለስና መጉላላት ለመቀነስ እንዲቻለው የደንበኞችን የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በማዘመን ከዚህ ቀደም ደንበኛው በአካል ተገኝቶ በሚያቀርበው የአገልግሎት ጥያቄ ተመስርቶ የሚሰጠውን አገልግሎት በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት (e-Services) ለማስተናገድ የሚያስችል ስርዓት ከኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባባር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ 21 (ሀያ አንድ ) አገልግሎቶችን ከሰኔ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለደንበኞች አቅርቧል፡፡
- Certificate Issuance of Non Genetically modified organisms (GMO)
- Competency license for environmental impact assessment (ESIA)
- Issuance of Competence Certificate for Flower Quality Assurance
- Competency license for chemical engineering
- Issuance of support letter for Logs Production and related service
- Issuance of support letter for Wood chipping and smoothing
- Issuance of Medicinal Plants Category/ Shiferaw, Moringa, Kesil and others exporter
- Issuance of support letter for Bamboo Export
- Issuance of Logs and Timber Exporter
- Issuance of Timber, Plywood and Related Products Exporter
- Issuance of support letter for Incense and Gums Products Exporter
- Issuance of Environmental Impact Clearance Permit
- Issuance of Support Letter for Spinning, Weaving and Completion of Plant Fiber
- Issuance of Support Letter for Preparation of Plant Fiber
- Issuance of Support Letter for Spinning, Weaving, wool and Completion of Animal Fiber products
- Information Desk for environment forest and climate change commission
- Issuance of support letter for Incense and Gums Products Importer
- Issuance of support letter for Forest Tree Seed Collection Business
- Issuance of support letter To germinate seedlings
- Issuance of Qualification for forestry development and related services
- Issuance of support letter To produce and export Briquette
ስለሆነም በአካባቢ ሆነ በደን ጉዳይ ፈቃድ እና የድጋፍ ደብዳቤ የምትፈልጉ ደንበኞች በተደጋጋሚ ወደ ኮሚሽን መ/ቤታችን በአካል መምጣት ሳያስፈልግ የሚከተሉ አድራሻዎችን፡-
1ኛ https://www.eservices.gov.et/provider/1065 ወይም
2ኛ https://www.eservices.gov.et/ ተጠቅማችሁ የአገልግሎት ጥያቄ በበይነ-መረብ (ONLINE) በማቅረብና በመከታተል ጉዳዩ ስለማለቁ ማረጋገጫ ሲደርሳችሁ አስፈላጊውን ማስረጃ በመያዝ ፈቃድ/የድጋፍ ደብዳቤ ለመውሰድ አንድ ግዜ ብቻ በመምጣት መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን መ/ቤታችን ከ ምስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እነዚህን አገልግሎቶችን በበየነ-መረብ አማካኝነት ብቻ የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ
- ለአካባቢ ዘርፍ ፈቃድ 0111-70-4064, 0111-70-4065, 0111-70-4023
- ለደን ዘርፍ ፈቃድ 0111-70-4134
- ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት 0111-70-4152 ይደውሉ