በ2013 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ 37 ሚሊዮን ብር ከደን ምርት ዝውውር ሮያሊቲ መሠብሰቡ ተገለፀ።
ጥቅምት 10/02/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
*********************®*********************
የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን በበጀት አመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በጽህፈት ቤታቸው መግለጫውን የሠጡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር ፕ/ር ፍቃዱ በየነ እንዳሉት በሩብ ዓመት ብቻ 37 ሚሊዮን ብር ከደን ምርት ዝዉዉር ሮያሊቲ ተሰብስቦ ለመንግስት ገቢ ሆኗል። በሩብ ቀጀት ዓመቱ በየዘርፉ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከልም የሚከተሉት ተጠቅሰዋል:-
1. የአካባቢ ልማትና ጥበቃን በተመለከተ:-
© በ1827 የልማት ተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ የአካባቢ ህግ አክብረው የሚሰሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የህግ ተከባሪነት ክትትልና ቁጥጥር ተካሂዷል፡፡መሰረታዊ የብክለት ችግር ያለባቸው ተለይተው ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተደርጓል፡፡
© ሁሉም የአካባቢና ማህበረሰብ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት የሚያስፈልጋቸው የልማት ፕሮጀክቶች ጥናቱን ሳያስጠኑ ወደ ልማት ሥራ እንዳይሸጋገሩ ለማድረግ ሰፊ ጥረት የተደረገ ሲሆን 1426 የልማት ፕሮጅክቶች በሩብ ዓመቱ የአካባቢና ማህበረሰብ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ይሁንታ አግኝተው ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
© የአካባቢ ብክለት በቀጥታ በዜጎች ላይ የሚያስከትለው የማህበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ታሳቢ እንዲሁም ብከለትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሁሉም ዜጋ ድርሻ ወሳኝነት መነሻ ጥቆማ የማቅረብ እንዲሁም አስረጂነት ሳያስፈልግ በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ መመሰረት የሚችሉበት የህግ ሥርዓት ዝግጅት ተከናውኗል።
© በማህበረሰቡ የብክለት ይወገድልኝ አቤቱታ ጥቆማዎች መነሻ የብክለት ምንጮችን ተለይተዉ 237 የብክለት ይወገድልኝ አቤቶታዎች በተለያየ ደረጃ ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
© የአካባቢ እንክብካቤ ሥራዎች እንዱ መሳሪያ ለሆነው የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ ቃድ 63 ልዩ ልዩ የሙያ እና ይሁንታ ፈቃዶች ተሰጥተዋል፡፡
2. የደን ሀብት ልማት፣ ጥበቃና እንክብካቤን በተመለከተ
© አገራዊ የደንና የጥበቃ ቦታዎች ሽፋንን ከማሳደግ ረገድ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አመራር ሰጪነት በተደረገዉ ርብርብ ባሳለፍነዉ ክረምት 5 ቢሊዮን ችግኝ የተተከለ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 3.562 ቢሊዮን የደን ችግኞች በ 771,795.66 ሄ/ር መሬት ላይ ተተክለዋል( 31 በመቶ የሚሆኑት የሀገር በቀል ዝርያዎች ናቸው፡፡)
© ለተተከሉት ችግኞች የእንክብካቤ ተግባራትን አስመልክቶ የአረምና የኩትኳቶ ስራ እየተከናወነ ሲሆን በነሀሴ ወር መጨረሻም በሞቱት ችግኞች የመተካት ተግባር ተከናዉኗል፡፡
© በዚህ በጀት ዓመት ለጎረበት አገሮች የሚደረገዉን ድጋፍ ጨምሮ 6 ቢሊዮን ችግኝ የሚዘጋጅ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 4 ቢሊዮን የደን ችግኝ የማፍላት ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ ሲሆን በዚህ ሩብ ዓመት ለዚሁ ተግባር የሚዉል 31.3 ቶን የተለያዩ የዛፍ ዝርያ ዘሮችን በማሰባሰብ እንዲሰራጭ ተደርጓል።
© ያሉንን የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ ደኖቻችንን ከመጠበቅ ረገድ17.22 ሚ/ሄ/ር ነባር የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ደኖችን የመጠበቅ፣ የመንከባከብና በዘላቂነት እንዲጠበቅ የማድረግ ስራ ተሰርቷል።
© በተጨማሪ 0.457 ሚሊዮን /ሄ/ር መሬት ላይ የሚገኙ የተፈጥሮ ደኖችን በአሳታፊ የደን አስተዳደር ስርዓት በማስገባት በዘላቂነት እንዲጠበቁና ተገቢውን ግልጋሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።
ከደን ዘርፉ የሀብት ግኝትን በማሳደግ ረገድ:-
© 37 ሚሊዮን ብር ከደን ምርት ዝዉዉር ሮያሊቲ ለማግኘት /ለማሰባሰብ ተችሏል፡፡
© 59 ሺ ቶን የደን ምርት ዉጤቶችን ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የተቻለ ሲሆን ወደ ዉጭ ከተላከው 2504.7 ቶን አጣና 7,499,670 የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም ከ185 ቶን ወደ ዉጭ ከተላከ እጣንና ሙጫ 611,059 የአሜሪካ ዶላር ማገኘት ተችሏል፡፡
© በዘርፉ ወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ለ320 ሺ ዜጎችን ጊዜያዊ የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 140,071 ሴቶች ናቸዉ፡፡
3. የአየር ንብረት ለውጥና የብዝሀ ህይወት ልማትና ጥበቃን በተመለከተ
© በ12 የዘርፍ መ/ቤቶች ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ሜይንስትሪም መደረጉን ለማረጋገጥ ታቅዶ፣ ምንም እንኳን በአንዳንድ ተቋማት የተሟላ ባይሆንም፣ በ12 የዘርፍ መ/ቤቶች ሜንስትሪሚንግ ተደርጓል።
© የሀገራችን ፍላጎትና አቋም የሚያሳዩ 2 የአካባቢ ስምምነት ሰነዶችን ተዘጋጅተው ለሴክሬታሪያቱ ተልከዋል።
© በ2 የዓለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነቶች ድርድር መድረኮች እና በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ ተሳትፎ በሚደረግባቸው ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጉዳይ ስብሰባዎችና ፎረሞች ለመሳተፍና የሀገራችን ፍላጎት እንዲንጸባረቅ ለማድረግ ታቅዶ በ2 የድርድር መድረኮችና ፎረሞች (UNFCCC & UNGA75) ላይ በቨርችዋል ተሳትፎ ተደርጓል።
© ሀገራችን በዓለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነቶች ድርድርና ተሳትፎ ያላትን የመሪነት ሚና ለማስቀጠል የLDCs Group እና AGN ቡድኖች በሚያዘጋጇቸው መድረኮች ላይ በቨርችዋል መሳተፍ ተችሏል።
© ወራሪ መጤ ዝርያዎች ለመከላከል ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የተዉጣጣ አንድ ግብረሃይል ተመስርቶ ስልት (Strategy) እየተዘጋጀ ይገኛለ፡፡ ከሚመለከታችው አካላት ጋር በመተባባር ወራሪ መጤ ዝርያዎችን የማስወገድ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።