በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ማህበረሰቡን ሊያነቃቃ እና ሊያሳትፍ በሚችል መልኩ መተግበር እንዳለበት ተገለፀ።
የካቲት 2016ዓ.ም - ሐዋሳ
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የ2016ዓ.ም የግማሽ ዓመት የአካባቢ ዘርፍ የስራ አፈፃፀም በሲዳማ ክልል ዋና ከተማ ሐዋሳ እያካሃደ ይገኛል።
በመድረኩ የሰው ልጅ ስልጣኔን ከጀመረበት ወቅት ጀምሮ በተፈጥሮ ሀብቶች እንዲሁም በአካባቢ ላይ የሚያሳድራቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ በመምጣታቸው ለዘርፉ ትኩረት በመስጠትና ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን የአካባቢ ስምምነቶች ተግባራዊ ማድረግ ላይ ሁሉም ባድርሻ አካላት የሚያሳትፍ ተግባር ላይ በቅንጅት መሰራት እንዳለበት ተነስቷል።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ለሊሴ ነሜ በመድረኩ ላይ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀፅ 44(1) መሰረት ዜጎች ንፁህና ለኑሮ ተስማሚ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት እንዳላቸው በመግለፅ ባለስልጣኑ የዜጎችን የአካባቢ ደህንነት መብቶችና ዓላማዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለማድረግ እና ሌሎች የአካባቢ ህጎችን እና አዋጆችን ተከባሪነትን የመከታተል እንዲሁም የድጋፍና ቁጥጥር ተግባራትን እየተከናወኑ መሆናቸውን በመግለፅ እና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መሪነት እየተተገበረ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጠናክረው ይተገባራሉ፡፡
ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በመቀጠልም በሚካሄደው የስራ አፈፃፀም ውይይት የታዪ መልካም አጋጣሚዎችን በማጎልበትና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በሁላችንም ርብርብ አረንጓዴና ከብክለት ነፃ ሆና ያደገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከወትሮው በተለየ አሰራርና አካሄድ በተሻለ ሁኔታ ማቀድና መፈፀም እንሚገባ ገልፅዋል ።