በኢትዮጵያ "የሰርኩላር ኢኮኖሚን" ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ።
ጥር/2014 ዓ.ም
አ ዲ ስ አ በ ባ
********************®********************
ፔትኮ(PETCO) ኢትዮጵያ የተሠኘና ለሠው ልጆች ፍጆታ ላይ የዋሉ የደረቅ ቆሻሻዎች ተረፈ ምርቶች በሰውና በአካባቢ ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ መልሶ ግልጋሎት ላይ ለማዋል እንዲቻል የሚሰራ ሀገር በቀል ድርጅት ከኖርዌይ የአብያተ ክርስቲያናት ትብብር (NCA) ጋር በመሆን በኢትዮጵያ "የሰርኩላር ኢኮኖሚን" ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን ስለሚሰሩበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ።
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው የስራ ሀላፊዎቹን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባወያዩበት ወቅት በእንግዶቹ እንደተገለፀላቸው "የሰርኩላር ኢኮኖሚን" ለመተግበር የህግ ማዕቀፎች ክፍተት መታየቱን በጥናት ማረጋገጣቸውን ገልፀው ክፍተቶችን በመቅረፍ በመስኩ ውጤታማ ስራን ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ የቋማቱ የስራ ሀላፊዎች ተወያይተው ከስምምነት ደርሰዋል። ለዚህም የጋራ ጥረት ይረዳ ዘንድ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከናወነው የህግ ማዕቀፎች ዳሠሳ ጥናት ግኝቶች ላይ ተመስርቶ ብሄራዊ ስትራተጂ እንዲዘጋጅ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
ከዚህም በተጨማሪ የኖርዌይ አብያተ ክርስቲያናት የልማት ትብብር የኢትዮጵያ ቢሮ በሀገሪቱ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ የደን ሀብቶች እንዲጠበቁ የሚረዳ ስትራተጂካዊ እርምጃን ለመተግበር የሚያስችል ፕሮጀክት መቅረፁን በመግለፅ ለስራው ተግባራዊነትም ከተቋማቱ ጋር በሚካሄደው ስምምነትና ተግባራዊ ስራ ላይ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስፈላጊውን ሚና እንዲጫወት ጥሪ ቀርቦ ከስምምነት ተደርሷል።