'' ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ'' በሚል አየተካሄደ የሚገኘው ሀገር አቀፍ የአካባቢ ብክለት ቅነሳ የግንዛቤ መፍጠሪያ ንቅናቄ ዘመቻ ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ ።
ሀምሌ 20/2016 ዓ.ም
አዳማ
****
ከመጋቢት ወር ጀምሮ በሀገር ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው የአካባቢ ብክለት ቅነሳ ንቅናቄ እስከ አሁን የተሰሩ ስራዎች የተገመገመ ሲሆን በንቅናቄውም የህብረተሰቡ ግንዛቤ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ::
የብክለት መግቻ ንቅናቄው የዜጎች ጤናማ አካባቢ የመኖር ህገ መንግስታዊ መብትን ለማጎናጸፍ ፣ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ የማይተካ ድርሻ ያለው በመሆኑ ፣ ሀገራዊ አጀንዳ በማድረግ በሀገራችን ከከፍተኛ አመራሮች እስከ ታችኛው የአስተዳዳር እርከን ድረስ ትኩረት በመስጠታቸው የተሻለ ውጤትና ልምድ መገኘቱን ተነስቷል ።
የብክለት ቅነሳ ንቅናቄው በአንድ ተቋም ብቻ የማይሰራ በመሆኑ ጉዳዩ በዋነኛነት የሚመለከታቸው ተቋማትንና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ፣ ከፌደራል እስከ ታችኛው አስተዳደር እርከን ድረስ በተነበበ ሁኔታ በመስራቱ የተሻለ ውጤት የተገኘ መሆኑንና በቀጣይ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተጠይቋል።
አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቁ ነገር ግን ሀገራዊ አጀንዳ በመሆኑ መልካም አጋጣሚ የተፈጠረ ስለሆነ ተባብረን ፣ጠንክረን ሰርተን ለውጥ ማምጣት የምንችለው ጊዜው አሁን በመሆኑ በቅንጅት መሰራት ያለበት መሆኑን ጭምር በውይይት መድረክ ላይ መግባባት ተችሏል።
በግምገማው ማጠቃለያም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውሃ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት እና የአካባቢቢ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የፕላንና በጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ የፌዴራል፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ ለምግብነት የሚሆን የችግኝ ተከላ በማካሄድ የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ሀገር አቀፍ ግምገማ መድረክ ተጠናቋል ።
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
ድረገጽ https://epa.gov.et/
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/@epa-ethiopia258
ቴሌግራም https://t.me/efcccethiopia
ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/epaethiopia
ኢ-ሰርቪስ https://www.eservices.gov.et/provider/1065