የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ውይይት እየተካሄ ነው።
ሀምሌ 19/2016 ዓ.ም
አዳማ
የ2016 ዓ.ም የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ የውሃ ፣መስኖ ፣ቆላማ አካባቢና የአካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊዎችና አባለት ፣ የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊዎች፣ የፌዴራል የዘርፍ መ/ቤቶች፣ የክልልና ከከተማ መስተዳድር የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊዎች የተሳተፉበት ውይይት እየተካሄ ነው ።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በህግ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሟላ መልኩ ለማሳካት ከሚመለከታቸው አካለት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ስልትና ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በመዘጋጀት እየሰራ እንደምትገኝ እና ከክልሎች እና ከከተማ መስተዳድሮች ጋር ወጥ የተናበበ ዕቅድና አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ፣አፈጻጸም በጋር በመገምገም እና ያጋጠሙ ችግሮችን በጋራ በመለየት እርምት እየተወሰደ በመሰረቱ በበጀቱ አመቱ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል ።
ወ/ሮ ፍሬነሽ አክለውም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ሰፊ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እንዲሁም የአካባቢ ደህንነት ህጎች ወጥተው ተግባራዊ መደረጉን አብራርተዋል ። በተለይም የከተማ የደረቅ በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ፣ የእንዱስትሪ ብክለት ፣ ከማምረቻ ተቋማት የሚወገዱ ተረፈ ምርቶች ፣ አደገኛ ኬሚካሎችና ቆሻሻዎች በሌሎች ቆሻሻዎች በአፈር ፣ በውሃ ፣ በአየር ሀብቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ብክለት የመከላከልና የቁጥጥር ስራዎች መሰራቱን ገልጸዋል ።
በሌላ በኩል ከውይይት መድረኩ በመጋቢት ወር በ2016 ዓ.ም "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ "በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የብክለት መግቻ የህዝብ ንቅናቄ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የአስተዳዳር እርከን ድረስ የሚገኙ አመራሮች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ በመሆኑ የተሻለ አፈጻጻም እየተመዘገበ እንደሚገኝ ተነስቷል ።
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ