Friday, 27 September 2024

የአካባቢ ጥበቃ የፕላነሮች ፎረም የዘርፉን የአንደኛ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም በጋራ ገመገሙ።

የአካባቢ ጥበቃ የፕላነሮች ፎረም የዘርፉን የአንደኛ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም በጋራ ገመገሙ።
EPA/ህዳር 3/2015 ዓ.ም፣ ቢ ሾ ፍ ቱ
************************®*******************
የፌዴራ፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የአካባቢ ጥበቃ የፕላን ኃላፊዎች ፎረም አካላት በተገኙበት የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የ2015 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ተገመገመ።
የዘርፉ ስራዎች እቅድና የስራ የስራ አፈፃፀም በሁሉም እርከኖች የተናበበ፣ የሚደጋገፍና ወጥነት ያለው እንዲሆን የፕላን ኋላፊዎች ፎረም ቀደም ብሎ የተቋቋመ ሲሆን የስራ ሀላፊዎቹ በተቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት በየደረጃው ያሉ የዘርፉ ተቋማት ስራ አመራሮች ለስራ አፈፃፀም ግምገማ ከመገናኘታቸው ቀድመው በቴክኒክ ደረጃ ግምገማና ግብረ መልስ የመለዋወጥ አሠራርን ይተገብራሉ።
 
 
የግምገማ መድረኩን በአካል ተገኝተው በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው ለስራ ሀላፊዎች እንዳሉት " የዘርፉ ዕቅድ እና ሪፖርት ወጥነት ያለውና ተናባቢ እንዲሆንና የዘርፉን ግቦች በውጤታማነት ለመተግበር በጋራ ማቀድና አፈፃፀሙን መገምገም እንዲሁም መግባባት በተደረሰበት የጊዜ መርሀ ግብርና የሪፖርት ፎርማት መሠረት ፎርማት ሪፖርት ይጠበቅበታል" ብለዋል።
ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ በመክፈቻቸው አክለውም ፎረሙ አንዱ ክልል ከሌላ የሚማርበትና ልምድ የምትጋሩበት መድረክ በመሆኑ በትኩረት ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
Follow us on:
Services:https://www.eservices.gov.et/provider/1065
Facebook: https://www.facebook.com/MefEth/
Telegram: https://t.me/efcccethiopia
Youtube:https://youtube.com/channel/UCz_C2Zik-Rjbo8MOyXrdtcQ
 
 

የባለስልጣንኑ አድራሻ

አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከአብርሆት ቤተመጻሕፍት በስተጀራባ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አጠገብ፣ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9

ስልክ፡ +251 (0)11-170-4038/4150

ፋክስ፡ +251 (0)11-170-4158/ 45

ኢመይል   Info@epa.gov.et

ቲውተር  https://twitter.com/epaethiopia

ፌስቡክ   https://www.facebook.com/MefEth/

ቴሌግራም   https://t.me/efcccethiopia

..      12760

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ