Friday, 27 September 2024

የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅድ ለማሳካት የዓለማቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።

የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅድ ለማሳካት የዓለማቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።
መጋቢት 22/2014 ዓ.ም
አ ዳ ማ
**************************®*********************
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎችን ለመቋቋም የሚያስችላትን አጠቃላይ ማዕቀፍ ያካተተውን ብሄራዊ የማጣጣሚያ እቅድ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ባገናዘበና ከተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፋዊ ስምምነት ፍላጎቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በማዘጋጀት ለሴክሬተርያቱ አስገብታለች። ይህ እቅድ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ከ2019 እስከ 2030 የሚተገበር ሲሆን እቅዱም አምስት ስትራቴጂካዊ የሆኑና ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የሚተገበሩ ጉዳዮችን እና 18 የማስተሰርያ አማራጮችን ለይቶ ያስቀመጠ ነው።
ኢትዮጵያ ቀደም ብሎም በመስኩ በርካታ ተግባራትን ስታከናውን የቆየች ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዕቅዱን የሙከራ ትግበራ ጀምራለች። የዕቅዱ የሙከራ ትግበራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፋዊ ስምምነት የገንዘብ ድጋፍ እና በአለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት ኢንስቲትዩት አስተግባሪነት በተመረጡ የሀገራችን ክፍሎች በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን የስራው አፈፃፀምም በየወቅቱ በብሄራዊ የአመራሮች የመማክርትና የባለሞያዎች ቡድን እየተገመገመና አስፈላጊ ድጋፎች ይደረግለታል፤ በዚህም ውጤታማ ስራ ስለመከናወኑ ተገልጿል።
በዚሁ ማዕቀፍ መሠረት በአዳማ ከተማ የስራውን አፈፃፀም በመማክርት ኮሚቴው ተገምግሟል፤ በግምገማውም አበረታች ውጤት ስለመኖሩ ተገልጿል። የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረኩን ተገኝተው የመሩት የኢትዮጵያ አካባቢ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው አፅንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት "ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቀውስን ለመከላከል እያደረገች ያለችው ቁርጠኝነት የማይናወጥ ነው" ብለዋል። ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁትም ኢትዮጵያ የታቀዱትን ስራዎች በተሻለ ሁኔታ ከግብ ለማድረስ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለዕቅዱ ማስፈፀሚያ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል" ብለዋል።ጥረት ሊደግፍ ይገባል ብለዋል።

የባለስልጣንኑ አድራሻ

አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከአብርሆት ቤተመጻሕፍት በስተጀራባ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አጠገብ፣ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9

ስልክ፡ +251 (0)11-170-4038/4150

ፋክስ፡ +251 (0)11-170-4158/ 45

ኢመይል   Info@epa.gov.et

ቲውተር  https://twitter.com/epaethiopia

ፌስቡክ   https://www.facebook.com/MefEth/

ቴሌግራም   https://t.me/efcccethiopia

..      12760

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ