Friday, 27 September 2024

የከፍታማ ቦታዎች የአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት

 

የከፍታማ ቦታዎች የአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት

  

1.    መግቢያ

 

በከፍታማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች ለአየር ንብረት ለዉጥ ተፅዕኖዎች ማለትም ለሙቀት መጨመር፣ ለከፍተኛ ቅዝቃዜና ውርጭ መከሰት፤ ከመደበኛ ያለፈ የዝናብ ስርጭት፣ የዝናብ ስርጭት መጠን ተለያይነት፣ ተደጋጋሚ የሆኑ የድርቅ ክስተቶች እና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የእርሻ መሬት ምርታማነት መቀነስ እንዲሁም የተፋሰሶች መመናመን bከፍተኛ ሁኔታ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

 

በመሆኑም በኢትዮጵያ ከፍታማ ቦታዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች ለአየር ንብረት ለዉጥ ተፅዕኖዎች ያላቸዉን ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲቻል መንግስት ዘርፈ ብዙ ምላሾችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም ዉስጥ አንዱ ከተባበሩት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር የተነደፈዉ የከፍታማ ቦታዎች የአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት ነዉ፡፡

 

2.  ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚሆኑባቸዉ ክልሎችና ወረዳዎች

 

ፕሮጀክቱ በአራት ክልሎችና በ8 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እነርሱም

                                      i.        በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስተዳደር እና ዳዋ ጨፋ ወረዳ ፣

                                     ii.        በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በያያ ጉለሌ ወረዳ እና በሰበታ ሃዋስ ወረዳ፣

                                    iii.        በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአፅቢ ወንበርታ እና በታሕታይ ቆራሮ ወረዳዎች እና  

                                    iv.        በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ እና በሃዋሳ ከተማ መስተዳድር ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡

 

3.  የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ እና ግቦች

3.1.    የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ

በሃገሪቱ የልማት ዕቅዶች ዉስጥ የአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ እርምጃዎችን የማካተት፣ በበጀት እንዲደገፉ ማድረግና የማቀናጀት፤ የአየር ንብረት ለዉጥ መረጃዎች ለየወረዳዎቹ ማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆኑ ማስቻል፣ የተሻሻሉና የአየር ንብረት ለዉጥን ያገናዘበ የግብርና ልማት ሥራዎችን የማስተዋወቅና የመስራት፣ የዝናብ ዉኃን ለማቆየት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራዎችን መስራት እንዲሁም የተለያዩ የገቢ ምንጮችን የመፍጠርን ዋና ዋና ሥራዎችን ይሠራል፡፡

 

 

3.2.    የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ግቦች

 

ፕሮጀክቱ ሦስት ዋና ዋና ግቦች ያሉት ሲሆን እነሱም

 

Ø  ግብ 1፡ በፌዴራል፣ በክልል፣ በወረዳ እና በማህበረሰብ ደረጃ የአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ ዕቅዶችን የማቀድ አቅምን ማጎልበት፤

 

Ø  ግብ 2አየር ጠባይ ለዉጥ ምክንያት የሚከሰት አደለን ለመቋቋም የሚያስችል የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታ መረጃ አጠቃቀምን ማጠናከር፣ እና

 

Ø  ግብ 3 የአየር ጠባይ ሁኔታን ያገናዘበ የእርሻ ስራና የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን በመተግበር የማህበረሰብ አባላትን የሥራ ዕድል እና የገቢ ምንጭ ማበራከት የሚሉት ናቸዉ፡፡

 

4.  የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ተግባራት

 

በፕሮጀክቱ ሊተገበሩ የታቀዱ ዋንኛ ተግባራት፤

 

·      የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር፣ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለዉጥ ሚኒስቴር እና የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጄንሲ የአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ እርምጃዎችን የማቀድና የማካተት፣ በበጀት እንዲደገፉ በማድረግ ረገድ ያለባቸዉን አጠቃላይ የአቅምና የሃብት ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የስልጠናና እና የቁሳቁስ ፍላጎትን መለየት፣

·      የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ የአቅም ማጎልበቻ ፕሮግራሞችን በፌዴራል፣ በክልል፣ በወረዳ እና በማህበረሰብ ደረጃ ለሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች መንደፍ፣

·      በግብርና እና በስነምህዳር ጥበቃ እና ልማት ዙሪያ ለሚደረጉ ሥራዎች የቴክኒካልና የስልጠና ማኑዋሎችን እና ቁሳቁሶችን ማዘጋጀትና ዉጤታማነታቸዉን መከታተል፣

·      በዩንቨርሲቲዎችና በሌሎች የምርምር ተቋማት መካከል የተለያዩ ተሞክሮዎችን እና ፈጠራዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ፎረም ማቋቋም እና ተከታታይ የልምድ ልውውጥና የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር የሚያስችል ተግባራትን ማከናወን፤

·      በአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ ዙሪያ ከሚሠሩ አለም አቀፍ ዩንቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ጋር ትስስሮችንመፍጠር የልምድ ልውውጥና የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር የሚያስችል ተግባራትን ማከናወን፤

·      የአየር ንብረት ለዉጥ የሚያስከትለዉን ተፅዕኖ እና ተገቢ የሆነ የአየር ንበረት ለዉጥ ማጣጣሚያ ተግባራት ያላቸዉን ፋይዳ በተመለከተ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን መከናወን

·      8ቱም ፓይለት ወረዳዎችአዉቶማቲክ የአየር ጠባይ መመዝገቢያ መሣሪዎች በመታገዝ  የአየር ንብረት ለዉጥ መረጃን በተለይም የየቀን፣ ሳምንታዊ እና ወቅታዊ ቦታ ተኮር የአየር ንብረት ትንበያዎችን በማዘጋጀት ለአርሶ አደሮች፣ ለሴቶች፣ ለወጣቶችና ለወረዳ የመንግስት አካላት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ተግባራትን ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጄንሲ ጋር በመቀናጀት ማከናወን

·      በሁሉም ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸዉ ወረዳዎች አንድ አንድ የአየር ንብረት ለውጥን ያገናዘበ የእርሻ ሥራ ሠርቶ ማሣያ ጣቢያን ማቋቋምና ለአርሶ አደሩ የልምድ መለዋወጫ ስፍራ አነዲሆን የማድረግ ሥራዎችን መከናወን፤

·      በሁሉም ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸዉ ወረዳዎች ቢያንስ አንድ የችግኝ ጣቢያ ማቋቋምና ያሉትን ማጠናከር፣

·      በሁሉም ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸዉ ፓይለት ቀበሌዎች የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራንና የደን ልማት ሥራን ማከናወን፤

·      በሁሉም ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸዉ ፓይለት ቀበሌዎች የተቀናጀ የተፋሰስ እና መልከአምድር የሚገኙ የግብርና ምርቶች የገበያ ዕድሎች እና ትስስር ዙሪያ ጥናት ማካሄድ፣ናቸው፡፡

 

5.  የፕሮጀክቱ የትግበራ ዘመን

 

ፕሮጀክቱ በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ2017 ሚያዝያ ወር ላይ የተጀመረ ሲሆን በ2022 ሚያዝያ ወር ላይ እንደሚያበቃ ይጠበቃል፡፡

 

6.  የፕሮጀክቱ  በጀትና የበጀት ምንጭ

 

የፕሮጀክቱ በጀት በጠቅላላ 6477000.00 (ስድስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ) የአሜርካን ዶላር ሲሆን ገንዘቡም በኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት አማካይነት ከአለም ኢንቫይሮሜንት ፋሲሊቲ ከተሰኘ የተባበሩት መንግሥታት የገንዘብ ተቋም በድጋፍ መልክ የተገኝ ነው፡፡

 

7.  የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች

 

በፕሮጀክቱ ትግበራ ዘመን በታችኛዉ የአስተዳደር እርከን ለሚገኙ አስፈፃሚ አካላት የሚደረጉ የተለያዩ የአቅምና የቁሳቁስ ድጋፍን ሳይጨምር በአራቱም ክልሎች በሚገኙ 8 ወረዳዎች በአጠቃላይ 55,000 /ሃምሳ አምስት ሺህ ተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፣

 

8.  እስከ ጥር 2011 ዓ.ም ድረስ በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች

 168 የኤክስቴንሽን ሰራተኞች እና 750 ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን የአየር ንብረት ለዉጥን ባገናዘበ የመሬት አያያዝ እና በኑሮ ማሻሻል ተግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰቷል፡

በስምንቱም ወረዳዎች በተቋቋሙት የግብርና መማማሪያ ማዕከላት ዉስጥ የሚካሄዱ የግብርና ሥራ መማማሪያ ሥራዎችን በማጠናከር በ5480 (ወ 2482 ሴ 2998) አርሶ አደሮችና በ189 የልማት ጣቢያ ሰራተኞች መካከል ጠንካራ የግንኙነት ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡ 

ü  በ8ቱም ወረዳዎች በዩንቨርሲቲዎችና በሌሎች የምርምር ተቋማት መካከል የተለያዩ ተሞክሮዎችን እና ፈጠራዎችን ለመለዋወጥ እንዲቻል በስምንቱም ወረዳዎች የምርምር ተቋማትን፣ ዩንቨርሲቲዎችን፣ የአርሶ አደር ቡድኖችን፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶችን ባሳተፈ መልኩ ፎረም የማቋቋም ሥራ ተከናዉኗል፡፡ የፎረም ማቋቋምን ተከትሎ የልምድ ልዉዉጥ ስብሰባ የተሄደ ሲሆን 649 (ወ 407 ሴ 202) አርሶ አደሮች ቦታ ተኮር የአየር ጠባይ መረጃ እንዲደርሳቸዉ ተደርጓል፡፡

 ü  የአካባቢዉን ሚዲያ በመጠቀም በስምንቱም ወረዳዎች ለሚገኙና ለ754,348 (ወ 380,289 ሴ 374,059) ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተሰርቷል፡፡

 ü  የአየር ንብረትን ያገናዘበ እርሻ እና በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ላይ በማተኮር በሁሉም ወረዳዎች ለሚገኙና 2726 (ወ 768 ሴ 1958) አርሶ አደሮች በአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ ቴክኒኮች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

 ü  የአዉቶማቲክ ዌይዘር ኤክስቴሽን እና የአየር ጠባይ መረጃን መሠረት በማድረግ የየቀን፣ ሳምንታዊና ወርሃዊ እንዲሁም ወቅታዊ የአየር ጠባይ መረጃን በማዘጋጀት ለ1746 ( ወ 938 ሴ 808) አርሶ አደሮችና 202 ( ወ 146 ሴ 56) የኤክስቴሽን ሰራተኞች ቦታ ተኮር የአየር ጠባይ መረጃ እንዲደርሳቸዉ ተደርጓል፡

 ü  በስምንቱም ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸዉ ወረዳዎች በሚገኝ በ1655 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ የአፈርና ዉኃ ጥበቃ ሥራዎች ተሰርቷል፡፡

 ü  በሁሉም ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸዉ በስምንቱም ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸዉ ወረዳዎች 16 ነባርና አዲስ የችግኝ ጣቢያዎች የተቋቋሙ ሲሆን ለችግኝ ጣቢያዎቹ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብኣቶች የቀረቡ ሲሆን የአጥር የማሳጠር እና እስቶር የመገንባት ሥራዎች ተጠናቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የችግኝ ጣቢያ ሰራተኞች የኮንትራት ሰራተኞች ቅጥር ተፈፅሞ 1,102,590 የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ ችግኖች ተፈልቷል፡፡

 ü  የአየር ጠባይን ያገናዘቡ የግብርና ቴክኖሎጂዎች በመለየት 2944 የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች የተሻሻሉ የድንች ዘር፣ የስንዴ፣ የገብስ፣ የቦቆሎ እና የቦሎቄ ዘር ግዥ በመፈፀም እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡

 ü  የገፀ ምድር አቀማመጥንና ቅርጽን በማስተካከልና የተለያዩ ለዉኃ ማቆር የሚረዱ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የዝናብ ዉኃን በማቆር አነስተኛ የመስኖ ልማት ሥራ በጓሮ ይዞታቸዉ ላይ እንዲያካሂዱ 210 ፕላሲቲክ ጆኦ መንብረን ግዥ በመፈፀም ለአርሶ አደሮቹ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 2 ኤስኤስ ግድብ ሥራ ተሠርቷል፡፡

  ü  ሮጀክቱ በሚተገበርባቸዉ ክልሎች የሚገኙ የውኃ ኢንተርፕራይዞችን እና በክልሉ የዉኃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮዎች ጋር በመቀናጀት 11 ጥልቅ የውኃ ጉድጓዶች ተቆፍሯል፡፡

  ü  በሁሉም ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸዉ አካባቢዎች ለሚገኙ ሴት አርሶ አደሮችና ወጣቶች በአጠቃላይ 2784 አርሶ አደሮች (ወ 637 ሴ 2147) በተለያዩ የአየር ንብረት ለዉጥ ማጣጣሚያ ተግባራትን በማቅረብ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

በግብይት ክህሎት ማሳደግ፣ እሴት መጨመርና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዙሪያ 3658 ሴት እና ለ45 ኤክስቴንስን ሰራተኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡         

 

የባለስልጣንኑ አድራሻ

አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከአብርሆት ቤተመጻሕፍት በስተጀራባ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አጠገብ፣ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9

ስልክ፡ +251 (0)11-170-4038/4150

ፋክስ፡ +251 (0)11-170-4158/ 45

ኢመይል   Info@epa.gov.et

ቲውተር  https://twitter.com/epaethiopia

ፌስቡክ   https://www.facebook.com/MefEth/

ቴሌግራም   https://t.me/efcccethiopia

..      12760

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ