ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮች ባለፉት ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ (የካቲት 10/2016 ዓ.ም ቢሾፍቱ)
ውጤታማነት በተቋም ውስጥ ለማጎልበት እና አመራሩን በዕውቀት፣ በስነምግባርና ብቃትን ማላበስ ወቅቱ የሚጠይቀው አብይ ተግባር ነው፡፡
የማነቃቂያ ርዕሶችን መሰረት ያደረጉ ንድፈ ሀሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር፣ እርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ፣ የተቋም ራዕይና ተልዕኮን ለማሳካት የጋራ አስተሳሰብ ማዳበር፣ የቡድን አስታሳሰብና አሰራርን ማጠናከር እንዲሁም የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ዓላማ አድርጎ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የተሰጠው ስልጠና ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሳው ብቁና በስነምግባሩ አርዓያ የሆነ አመራርን መገንባት የሚያስችል እንደነበር በመግለፅ የታለመለትን ግብ ያሳካ ነበር ብለዋል፡፡
ክብርት ዋና ዳይርክተሯም አያይዘውም የተሰጠው ስልጠና በመጠቀም በተነቃቃ መንፈስና በተነሳሽነት እንደተቋም የተቀመጠውን ዕራይና ተልዕኮ ለማሳካት አመራሩ ራሱን በየጊዜው እያበቃ ያገኘውን ስልጠና ወደ ፈጻሚዎች በማውረድ የተጀመሩ ስራዎችን በውጤታማነት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ በመጨረሻም ስልጠናው እንዲሳካ በአሰልጣኝነት፣ በአስተባባሪነት እንዲሁም በሰልጣኝነት ተገኝተው ስልጠናው ስኬታማ እንዲሆን ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበው የአቅም ግንባታ ፕሮግራሙ በይፋ መዘጋቱን አብስረዋል፡፡